ሀገር የምትበለጽገው በእድልና በችሮታ ሳይኾን በጥረትና በታታሪ ትውልዶች አቅም ነው፡፡
ብራውን ፉድስ ፋብሪካ የመሥራትና የመቻል ብሎም የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የበለጸገ የምግብ ሥርዓት በማቅረብ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ነው።
ፋብሪካው እንደ ክልል የኢኮኖሚ አቅም ከማጎልበት ባሻገር የፋብሪካዎች የግብዓት አቅርቦት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን ያስቀረና እዚህ ተመርቶ እዚሁ ወደ ፋብሪካ የሚገባ ምርት መጠቀሙ ከፍተኛ ሚና አለው።
ሀገር በቀል ሰብሎችን በመጠቀም የተመጣጠነ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል የሚሠራ ነው።
በተለይም የበቆሎ ምርትን ዋነኛ ግብዓት በማድረግ ልዩ ልዩ የበቆሎ ምግቦችን፣ የህጻናት ምግብ እና የበቆሎ ዱቄትን በማምረት የአመጋገብ ባሕልን የሚያሻሽል ነው፡፡
እንደ ሀገር ግዙፍ የኢኮኖሚ ምንጭ በሆነው የግብርና ምርት ላይ ያተኮረ መኾኑ ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን የበለጠ የሚያጠናክር ነው።
የብራውን ፉድስ ፋብሪካ በግብርና ዘርፍ የሚመረቱ ግብዓቶችን የሚጠቀምና የበለጸገ የምግብ አቅርቦትን የሚያሳድግ ነው።
ፋብሪካው የክልሉ መንግስት የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ የያዘው የፖሊሲ አካል ነው።
ፍትሃዊ የሃብት ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ሰፊ አበርክቶ አለው።
እንደሀገር ያለውን የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራን የሚደግፍና የክልሉን አጠቃላይ ልማት ለማሳደግ ሕዝቡ ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ በሳል አመራር መስጠት ይገባል።
ፋብሪካው ከዕለት ቀለብ ፍጆታ በዘለለ ግብዓት የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን የሚያፈራ እና የሥራ ባሕልን የሚቀይር ነው።
ለፋብሪካ ግብዓቶችን የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ማፍራት እና የሥራ ባሕልን የሚቀይር ነው።
የአማራ ክልል እምቅ ሃብትና ሰፊ የሰው ኃይል ባለቤት በመሆኑ የግል ባለሃብቶችን በማስተሳሰር የሚፈለገውን የኢኮኖሚ ደረጃ ማምጣት ይቻላል።
የክልሉን ኢንዱስትሪ ልማት ለማጠናከርና ሰፊ የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

