የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

የሰሜን ሸዋ ዞን በኢንዱስትሪ ልማት ማበብ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ግዙፍ ተደማሪ አቅም ነው።

ዛሬ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙትን የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርክ፤ የሴራሚክ ፋብሪካ እና የፐልፕ የወረቀት ፋብሪካዎችን ተመልክተናል፡፡

እነዚህ ግዙፍ ፋብሪካዎች በኢንዱስትሪ ዘርፍ የጀመርነው ሃገራዊ ሪፎርም እና ትግበራ ውጤት እየታየበት ለመሆኑ ህያው ምስክሮች ናቸው።

ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት የያዘችው የአምራች ዘርፍ በባህሪው የሃብት ብዜት እና የዘርፎችን ትስስር የሚፈጥር ነው።

በሰሜን ሸዋ ዞን የተመለከትናቸው ፋብሪካዎች አምራች በመሆናቸው አዲስ ሃብትን ወደ ኢኮኖሚው ይደምራሉ፡፡

በዘርፎች ትስስርም የአንዱ ምርት ለሌላው ግብአት የሚሆንና በተለይ በስራ እድል ፈጠራ እና የውጭ ምንዛሬን በማዳኑ በኩል ትልቅ ሚናን የሚወጡ ናቸው፡፡

ሰላም እና ትጋት ካለ ፋብሪካዎች ለልማት፤ ዜጎች ለለውጥ ሃገርም ወደ ዘላቂ ብልጽግና እንደምትራመድ የሰሜን ሸዋ ዞን ማሳያ ናት፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top