በባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቀርብ መወሰኑ ተገለፀ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ በመንግስት ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት በተመለከተ የተደራጀ የውሣኔ ሃሳብ አጥንቶ እንዲያቀርብ መስተዳድር ምክር ቤቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሰርቪስ አገልግሎት እየሰጡ ካሉት 21 ተሽ

E-mail Print PDF

የመርሣ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለወልዲያ ዩኒቨርስቲ ተሰጠ

የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት አራተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የመርሳ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጂ የወልዲያ ዩኒቨርስቲ እንዲጠቀምበት ወሰነ።

ምክር ቤቱ የቀረበውን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በማንሣት ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ የወልዲያ ዩኒቨርስቲ የአግሮ ኘሮስሲንግ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ከመመረጡ ጋር ተያይዞ ከሚኖረው ጠቀሜታ አኳያ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችል በቂና ለመርምር አመች  የሆነ ቦታ ለማግኘት የሚያስፈልገው መሆኑን አምኖበታል።

በመሆኑም ዩኒቨርስቲው ከዚህ በፊት በ2004 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ሂደቱን በመርሳ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የጀመረ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት 7100 ተማሪዎችን ተቀብሎ የአግሮ ኘሮስሊንግ የልህቀት ማዕከል በመሆን የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲያከናውን ለማስቻል ኮሌጁ ለዩኒቨርስቲው በቋሚነት መሰጠት እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በመጨረሻም  ኮሌጁ መሰተዳድር ም/ቤቱ  ለዩኒቨርስቲው ሲሰጥ የአካባቢውን ህ/ሰብ የቴከኒክና ሙያ ተጠቃሚነት ዕድል የሚያሣጣ እንዳይሆን ለማድረግ አሁን እየተሰጠ ያለው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጁ ስልጠና ጐን ለጐን መቀጠል እንዳለበትና የወልዲያ ዩኒቨርስቲም ወረዳው በሚያመቻቼው ቦታ ላይ ምትክ ቴክኒክና የሙያ ኮሌጅ ገንብቶ ለአካባቢው ህብረተሰብ እንዲያስረክብ ወስኗል።

 

የዳያስፖራና የህዝብ ግንኙነት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት

 
Content View Hits : 8411813

Comments

  • I like looking through a post that will make peopl...
  • you're in reality a excellent webmaster. The web s...
  • Amazing blog! Do you have any suggestions for aspi...
  • Hello! I could have sworn I've been to your blog b...
  • I do not even understand hoow I finisyed up right ...

Latest News

Who is online

We have 28 guests online

Entertainment