ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 3,486 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ም/ቤቱ ወሰነ

E-mail Print PDF

ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 3,486 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ም/ቤቱ ወሰነ

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት 4ኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ነሐሴ 20/2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ማሣኪያ ኘሮጀክቶች የሚሆን 3,486 ቢሊዮን ብር ወስኗል።

ውይይቱ የተጀመረው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ የምዕተ ዓመቱን ግቦች ማስፈፀሚያ በጀት ድልድል አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ሲሆን ማስፈፀሚያ የተመደበው ብር 3,486 ቢሊዮን እንደሆነና ይህም ለድህነት ተኮር ሴክተሮች የሚመደብ መሆኑን ገልፀው ቢሮው የበጀት ዕቅዱን አዘጋጅቶ ያቀረበበትን አግባብ በማብራራት ከ2006 ዓ.ም አፈፃፀም የ6ቱን ሴክተሮች ግምገማ መነሻ ያደረገ መሆኑን በዚህም የተጀመሩ ካፒታል ኘሮጀክቶች ብዙዎች ባለመጠናቀቃቸው በየአካባቢው ለመልካም አስተዳደር ችግር ምክንያት መሆናቸውን በግምገማቸው ማየታቸውንና ለዕቅድ መነሻ ማድረጋቸውን ውይይቱን መሠረት በማድረግም በቅድመ ዝግጅት የተሠሩ ስራዎች ያጋጠሙ ችግሮችና ለ2007 በጀት ዓመት ታሳቢ የተደረጉ ጉዳዮች ለማካተት ጥረት መደረጉን ዘርዘር አድርገው አብራርተዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበውን ማብራሪያ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስቶ በስፋት ከተወያየ በኋላ የ2007 በጀት ዓመት ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ማስፈፀምያ የተመደበውን በጀት የተለየ ትኩረት በመስጠት ለማከፋፈል በቢሮው በኩል የተደረገው ጥረት በተለይም በዋናነት ነባር ካፒታልና ኘሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እንዲውል የተያዘው አቅጣጫ ጥሩና ተገቢ መሆኑ ላይ በመስማማት በጀት ድልድሉ ሊታይ ይገባል ያላቸውን ማሻሻያዎች አስቀምጧል።

ለዋሊያ የካፒታል ፋይናንስ አቅራቢ ድርጅት ተጨማሪ ካፒታል ማሳደጊያ የአክሲዮን መዋጮ ከተመደበው ብር 200ሚሊዮን ውስጥ ብር100 ሚሊዮን ተቀንሶ ለሌሎች ሴክተር ኘሮጀክቶች ይዋል በሚል ሃሣብ ተስማምቶ የተቀነሰውን ብር ከ100 ሚሊዮን ውስጥ 50 ሚሊዮን ብር ለትምህርት ብር 30 ሚኒዮን ለውሃ እና ብር 20 ሚሊዮን ለጤና ሴንተር ኘሮጀክት በመደልደል የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች የዕቅድ ሃሣብ በተሰጠው ማስተካከያ መሠረት ተግባራዊ እንዲሆኑ አጽንኦ  በመስጠት ወስኗል።

 

የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ጉዳዮችዳሬክቶሬት

 
Content View Hits : 8450619

Comments

  • Heya і am for the primary time here. I fⲟund this ...
  • What's up, yeah this paragraph is really nice and ...
  • hey there and thank you foor your infotmation – I ...
  • This piece of writing provides clear idea designed...
  • Have you evеr thought about incⅼudiing a little bi...

Latest News

Who is online

We have 33 guests online

Entertainment