ቅላጅ ከገጠሩ ቀበሌ ተለይታ ራሷን ችላ የከተማ ቀበሌ እንድትሆን የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ወነሰ

E-mail Print PDF

ቅላጅ ከገጠሩ ቀበሌ ተለይታ ራሷን ችላ የከተማ ቀበሌ እንድትሆን የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ወነሰ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ብሎም በክልላችን የገጠር ቀበሌዎች ዘመናዊነትን በመላበስ መንግስትም በሰጠው የመሠረተ ልማት ግንባታ ማሟላት ልዩ ትኩረት በርካታ የገጠር ቀበሌዎች ራሳቸውን ችለው የከተማ ቀበሌ ኖሯቸው በመሪ መዘጋጃ ቤት እየተመሩ ይገኛሉ።

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የካቲት 7/2006 ዓ.ም ባካሄደዉ 4ኛ አመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የገጠር ቀበሌ የሆነችዉ ቅላጅ የከተማ ቀበሌ እንድትሆን የቀረበዉን ጥያቄ ተመልክቷል።

ቅላጅ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የዚገም ወረዳ ዋና ከተማ ስትሆን የገጠር ቀበሌ አካል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ እያጋጠማት ካለው የከተማ ልማት ስራ ላይም ሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አንፃር ራሷን የቻለች የከተማ ቀበሌ እንድትሆን የቀረበው ጥያቄ የረጅም ጊዜ ጥያቄ መሆኑ በኢኮኖሚ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ተገልጿል።

መስተዳድር ምክር ቤቱም የቀረበውን ማብራሪያ እና የውሳኔ አስተያየት መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ ቋሚ ኮሚቴዉ መርምሮ ባቀረበዉ ሃሳብ ላይ በመስማማት የዚገም ወረዳ ማዕከል የሆነችው ቅላጅ ራሷን ችላ የቀበሌ ከተማ ሆና እንድትቋቋም ወስኗል።

 
Content View Hits : 8439019

Comments

  • Youu can even barter the numbers with thee anxious...
  • Hi to all, the contents present at this web site a...
  • I am sure this piece of writing has touched all th...
  • For latest information you have to visit web and o...
  • Very good post! We will be linking to this particu...

Latest News

Who is online

We have 30 guests online

Entertainment