ያልተማከለ አስተዳድር ስርዓት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ማህበራዊ ፍትህን

E-mail Print PDF

ያልተማከለ አስተዳድር ስርዓት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ የሚደረገውን ጥረት በእጁጉ ያፋጥናል ተባለ

ሚያዚያ 21/1998 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወሰነው መሠረት የኢፌድሪ ህገ-

መንግስት የፀደቀበትን ቀን ህዳር 29 ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ በተለያዩ ክልሎች በአገር አቀፍ እየተከበረ ይገኛል። በመሆኑም በዚህ ዓመት ህገ -መንግስታችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል በሶማሊያ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ለ8ኛ ጊዜ ተከብሯል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሠራተኞችም ህዳር 30/2006 ዓ.ም የ8ኛው ብሔር፣ ብሔረሰቦችን በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ የፖናል ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የውይይቱን መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የጽ/ቤቱ ባለሙያ አቶ አበባው አለምነህ ናቸው። እርሳቸውም በተዘጋጀው ጽሑፍ መሠረት የህገ-መንግስታችን መሠረት የህዝቦችን ጥቅም ባረጋገጠ መልኩ የተመሠረተ እና በተለይም ስቪል ስርቫንቱ የሚጠበቅበትን ህገ-መንግስታዊ ግዴታ እና ማግኘት የሚገባውን መብት በዝርዝር አቅርበዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ያልተማከለ አስተዳደር ስርዓት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ የሚደረገውን ጥረት ያፈጥናል ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የህዝቦችን ማንነት ከነተፈጥሮአዊ ባህሪው ጠብቆ ለማቆየትና

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ታሪካቸውንና ወጋቸውን መልካም እሴቶቻቸውን ያልተማከለው አስተዳደር የሚፈጥርላቸውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው እንደ አግባብነቱ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ናቸው ሲሉ ተሣታፊዎች አክለው ገልፀዋል።

የፖናሉ ውይይት ተሳታፊዎች በከፊል

ያለተማከለ አስተዳደር ብዙ የቢሮክራሲ ውጣ ወረዶችን ያቃለለ መሆኑን በተጨባጭ ያየንበትና እየተሰራበት ያለ ጉዳይ መሆኑን ያስረዱት የውይይቱ ተሣታፊዎች በተማከለው ስርዓት ወቅት ቀበሌ ላይ የሚፈጠርን ችግር የሚያቀርቡት በማዕከላዊነት ለሚገኘው አካል በመሆኑ ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበት እና በጊዜ ሰፊ ተጐጅ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፤ አብዛኛውን ደግሞ ችግሩን እንደያዙ ታፍነው ይኖሩ ነበር ሲሉ አብራርተዋል።

 

 

 
Content View Hits : 8439016

Comments

  • Youu can even barter the numbers with thee anxious...
  • Hi to all, the contents present at this web site a...
  • I am sure this piece of writing has touched all th...
  • For latest information you have to visit web and o...
  • Very good post! We will be linking to this particu...

Latest News

Who is online

We have 30 guests online

Entertainment