የአማራ ክልል እና የቢንሻንጉል ጉምዝ ክልል የጋራ የልማት ትብብር

E-mail Print PDF

የአማራ ክልል እና የቢንሻንጉል ጉምዝ ክልል የጋራ የልማት ትብብር የአቻ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2006 እቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ

የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አየነው በላይ ሲሆኑ በንግግራቸውም በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈረመውን የጋራ የልማት ትብብር ሰነድ መሰረት ያደረገ የአቻ ቢሮዎች እቅድ ሲሆን ይህም ከአሁን በፊት ከነበረን የጋራ የልማት ትብብር ለየት የሚያደርገው እቅዱ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ዘንድ በበጀት መደገፉ ነው ብለዋል።

 

የሁለቱ ክልል አመራሮች ሲያወያዩ

አቶ አየነው ከዚህ ጋር አያይዘው እንደተናገሩት የሁለቱ ክልል አቻ ሴክተር ቢሮዎች በጋራ ያዘጋጀነውን እቅድ ወደ ተግባር በመቀየር ሀገራችን የያዘችውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ ይገባናል። በመሆኑም በእወቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የዳበረ ትብብር በማድረግ ለውጤት እንትጋ፤ መልካም ውይይት በማለት በይፋ ውይይቱን ከፍተዋል።

ጥቅምት 21/2006 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የሁለትዮሽ የጋራ የልማት ትብብር አቻ ሴክተር መ/ቤቶች በጋራ ያዘጋጁትን ዕቅድ መሰረት በማደረግ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስችላል፤ ያሉት የሁለትዮሽን እቅድ አጠቃለው ያቀረቡት የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ልዩ ረዳት አቶ ያረጋል አስፋው ናቸው።

በመሆኑም የቀረበውን የጋራ ዕቅድ መሰረት በማድረግ ሁለቱ ጎረቤታማ ክልሎች አንዱ ላንዱ በመደጋገፍ ያለውን ችሎታና ክህሎት በጋራ በመጠቀም የቆየውን የሁለቱ ክልሎች ቱባ ባህል በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት በዋነኛነት ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ተሳታፊዎች በአስተያየት አስምረውበታል።

በዚህ የጋራ ውይይት የሁለቱ የቢሮ ኃላፊዎችና ምክትሎቻቸው የተገኙ ሲሆን በሁለቱ አጎራባች ክልሎች የሚነሱ የህዝብ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ኮንፈረንስ ማካሄድ የቀበሌዎች፣ የወረዳዎችንና የዞኖችን የጋራ ግንኙነት በማጠናከር መስራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ተደርሷል።


 

 

 

Last Updated on Friday, 17 January 2014 12:29  
Content View Hits : 8450536

Comments

  • What's up, yeah this paragraph is really nice and ...
  • hey there and thank you foor your infotmation – I ...
  • This piece of writing provides clear idea designed...
  • Have you evеr thought about incⅼudiing a little bi...
  • Have you evеr thought about incⅼudiing a little bi...

Latest News

Who is online

We have 43 guests and 1 member online

Entertainment