የገጠር ሥራ-አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማሰማራት የንቅናቄ እቅድ ተዘጋጀ

E-mail Print PDF

የገጠር ሥራ-አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማሰማራት የንቅናቄ እቅድ ተዘጋጀ

በገጠር የሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶችን የሥራ ተነሳሽነት፣ ሥራ ፈጠራ ችሎታ በማጐልበት፣አደረጃጀቶቻቸውን በማጠናከር፣ የግብዓትና አቅርቦት ችግሮችን በመቅረፍ ወጣቶች በኢኮኖሚ ልማት በንቃት ተሣታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የንቅናቄ እቅድ ተዘጋጀ።

የአማራ ክልል መስተዳድር ም/ቤት ህዳር 20/2006 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የገጠር ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማሰማራት በቀረበው እቅድ ላይ የውይይቱን መነሻ ያቀረቡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ በማብራሪያቸውም በክልሉ ውስጥ ወደ 5.3 ሚሊዮን የሚገመት ወጣት ሃይል እንዳለና ከዚህም ውስጥ አብዛኛው በገጠሩ የሚኖር ነው፤ በመሆኑም ይህንን ሀይል ወደ ሥራ ማስገባት የተጀመረውን የእድገት ግስጋሴ ያፋጥናል ብለዋል። ስለሆነም በያዝነው በጀት ዓመት ንቅናቄው መጀመር እንዳለበትና ለዚህም በየደረጃው ያለ አመራር ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ሥራው በጥራትና በእውቀት መመራት ይገባዋል ሲሉ አክለው ገልፀዋል።

በአጀንዳው ላይ ለአስረጅነት የቀረቡት ወ/ሮ ፈንታየ ጥበቡ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና አቶ ዳኛቸው በየነ ከማዕድንና ኢነርጅ ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሲሆኑ የንቅናቄ ዕቅዱን ዓላማና ዋና ዋና ግቦች፣ በግብርና እና ግብርና ነክ ባልሆኑ ዘርፎች የሚፈጠሩ የሥራ እድሎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

መስተዳድር ም/ቤቱም የንቅናቄ እቅዱ በገጠር ያለውን ችግር ከመቅረፍ አኳያ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሚታው የጐላ በመሆኑ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ልዩ ትኩረት ተሰጦቶት እንዲሠራ ውሳኔ አሳልፏል።

Last Updated on Wednesday, 15 January 2014 13:59  
Content View Hits : 8450620

Comments

  • Heya і am for the primary time here. I fⲟund this ...
  • What's up, yeah this paragraph is really nice and ...
  • hey there and thank you foor your infotmation – I ...
  • This piece of writing provides clear idea designed...
  • Have you evеr thought about incⅼudiing a little bi...

Latest News

Who is online

We have 33 guests online

Entertainment