የባህርዳር ጊዮን እና የጐንደር ተራራ ሆቴሎች በአዲስ መልክ እንዲገነቡ ተወሰነ

E-mail Print PDF

ዜና መስተዳደር

የባህርዳር ጊዮን እና የጐንደር ተራራ ሆቴሎች በአዲስ መልክ እንዲገነቡ ተወሰነ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት መስተዳደር ምክር ቤት ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ አመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የባህርዳር ጊዮን እና የጐንደር ተራራ ሆቴሎች በአዲስ መልክ እንዲገነቡ ውሳኔ አስተላልፏል።

የባህርዳር ጊዮንና የጐንደር ተራራ ሆቴሎች ክልሉ ከኘራይቬታይዜሸን ኤጀንሲ ከተረከበ በኋላ ለዘላቂ ልማት ለማዋል እንዲቻል ኮሚቴ በማዋቅር ጥናት እንዲደረግ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ጥናቱ ተጠንቶ በኢንዱስትራና ከተማ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት ቀርቧል።

ጥናቱም ሁለቱ ሆቴሎች አሁን ያሉበትን ሁኔታ በስፋት የዳሰሳና ለዘላቂ ልማት ለማዋል የሚያስችሉ አማራጮችን ያመለከተ እንደሆነ ምክር ቤቱ በመግለፅ በጥናት ተደግፎ ውሳኔዎችን ማሳረፍ አዋጭና ዘለቄታዊ ጠቀሜታ እንዳለውም አክለው ገልፀዋል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የቀረበውን ማብራሪያ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስቶ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ የጥናቱ ሰነድ አጥኝ ኮሚቴው በበሰለ መልኩ ታይቶ የቀረበ መሆኑ ላይ በማስማማት

የባህርዳር ጊዮን ሆቴል ያረፈበት ቦታ ለባህርዳር ከተማ ብሎም ለክልሉ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሙሉ አለም የባህል ማዕከል አቅጣጫ የሚመጣውን መንገድ ወደ ጣና ሀይቅ ዳርቻ ድረስ የሚያደርስ ደረጃውን የጠበቀ መንገድ በመክፈት ቦታው ላይ ደረጃውን የጠበቀ ኢንተርናሸናል ሆቴል እንዲገነባና ግንባታው ሲፈፀምም ህበረተሰቡ በህይቁ የመጠቀም መብት እንዳይገደብና ሀይቁ እንዳይበከል አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ጐንደር ከተማ የበርካታ ቱሪስት መዳረሻ ከመሆኗ አንፃር በቂ ሆቴሎች ባላመኖራቸው የጐንደር ተራራ ሆቴል በአዲስ መልክ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል እንዲገነባበት ምክር ቤቱ ወስኗል።

በአብከመ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት

በህዝብ ግንኙነት ዋና የሥራ ሂደት የተዘጋጀ

Last Updated on Friday, 01 November 2013 11:53  
Content View Hits : 8439074

Comments

  • My spouse and I stumbled over here from a differen...
  • We imagine iin ssupplying what a buyer asks for. F...
  • Youu can even barter the numbers with thee anxious...
  • Hi to all, the contents present at this web site a...
  • I am sure this piece of writing has touched all th...

Latest News

Who is online

We have 42 guests online

Entertainment